ስለ ጃንደረባው ድኅረ ገፅ
የተወደዳችሁ የዚህ ድኅረ ገፅ ተከታታዮች ወገኖቻችን፣ ጃንደረባው በሚል ስያሜ የምናስተላልፈውን የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ስናስተዋውቅ እጅግ በጠም ደስ እያለን ነው።
ይህ ድኅረ ገፅ በሐዋርያት ሥራ ም 8,26-40 ለተጠቀሰው ኢትዮጵያዊና ክርስትናን ወደ ሀገራችን ላስገባው ባኮስ በመባል ለሚታወቀው ሰው መታሰቢያው ይሆንልን ዘንድ በመጽሐፍ ቅዱስ በሚታወቀው የማዕረግ ስሙ ጃንደረባው ብለን ሰይመነዋል።
ይህ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ በመዘኑ ለነበረችው ኢትዮጵያዊት ንግሥት ሕንደኬ የገንዘብ ሚንስቴር የነበረ ባለ ሥልጣን ነው።
ለአምላኩ (ለእግዚአብሔር) ከነበረው ታላቅ ፍቅር የተነሣ 5000ኪ ሜ በላይ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሳለም በየዓመቱ በመጓዝ አምልኮቱን ይፈጽም ነበር። በመጨረሻ ኢየሩሳሌምን ተሳልሞ ወደ ሀገሩ ሲመለስ፣ በሰረገላው ተቀምጦ ሲጠበቅ ስለነበረው የዓለም አዳኝ መሲህ ክርስቶስ የሚናገረውን መጽሐፈ ኢሳይያስን እያነበበ በመጓዝ ላይ ነበር። ከዚያም ድንገት ሳያስበው በመልአከ እግዚአብሔር ጥሪና በመንፈስ ቅዱስ ምሪት፣ በወንጌላዊ ፊልጶስ በኩል ወንጌል ተሰብኮለት ፣ አምኖና ተጠምቆ ክርስትናን ወደ ሀገራችን ያስገባልን ታላቅ አባት ነው።
ስለሆነም የዚህ ድኅረ ገፅ ዓላማ አባታችን ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ እንዳስተላለፈልንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማርቆስ 16,15-16 ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ፣ያመነ የተጠመቀ ይድናል፣ ያላመነ ግን ይፈረድበታል። ብሎ ደቀ መዛሙርቱን ባዘዘው መሠረት፣ እኛም ይህን በመከተል የወንጌልን መልእክት ለወገኖቻችን በጽሁፍና በአውድዮ፣ እንዲሁም በቢድዮ ቀላልና ግልጽ በሆነ መንገድ ለማስተላለፍ ነው።