Janderebaw

መግለጫ

በቤተ ክርስቲያንና በዓለም ላይ የሚታየውን ትርምስ ሊያረግብና ሰላምን ለማምጣት የሚቻልበት ብቸኛው መንገድ ፣ በስከብተ ወንጌል ሕዝቡን መድረስና ማገልገል ሲቻል ብቻ እንደሆነ እናምናለን፣ ማለትም ከቃሉ የተነሣ ሰላም በሕዝቡና በቅዱሳኑ መካከል መስፈን ስለሚችል ነው።

ወንጌል በግልጽ ከተሰበከና የሰው ልጅ ፈቃደኛ ሆኖ ቃሉን ከሰማ ፣ ሕይወቱ ስለሚለወጥ፣ ሰላም በአድማጮቹ ዘንድ ይሰፍናል። በስዎች ዘንድ ሰላም ከሰፈነ ፣ በቤተ ክርስቲያንም ሰላም ይነግሣል ማለት ነው። ቤተ ክርስቲያን የሚለው የቃሉ ትርጓሜ የክርስቲያኖች (የምእመናን)ኅብረት ማለት ነውና።

ተስፋ የምናደርጋትን ሰማያዊት የእግዚአብሔር መንግሥት መውረስ የምንችለው በትምህርተ ወንጌል ታንጸን፣ ንስሐ በመግባት፣ የነፍሳችን አዳኝና ቤዛ በሆነው በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን ብቻ እንጂ በመለያየትና በመወጋገዝ ፣ ብሎም እኔ የጳውሎስ፣ አንዱ የአጵሎስ፣ ሌላው ደግሞ እኔ የኬፋ ብሎ በመከፋፈል አይደለምና። 1ቆሮ 1,12-13

የሚገነባና የሚያንጽ ፣ ሰዎችን ወደ ሰላምና ወደ አንድነት የሚያደርስ የወንጌል መልእክት ከተላከልን ለማስተናገድ ዝግጁዎች ነን።

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን።